Call Us for support!

251112783827

251911770203

        This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Visitors Counter

10966050
TodayToday12481
YesterdayYesterday14452
This_WeekThis_Week12481
This_MonthThis_Month100000
All_DaysAll_Days10966050
Yanet Health and Business college
Medical laboratory Services
Full-fledged Labratory Equpments
Yanet Health and Business college
Experienced Teachers
Yanet Health and Business college
Full-fledged Demonistration Facility
Yanet Health and Business college
Disciplined Students
Yanet Health and Business college
ICT lab and WiFi internet
Yanet Health and Business college
We Graduated students for 8th time and we are Celebrating our 10 year Anniversary
Yanet Health and Business college
Addis Ababa (Mesalamiya Sefere selam Nigusie Turfe Building)

 

 

ያኔት የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ  መተዳደሪያ ውስጠ ደንብ የሰልጣኞች  መብትና ግዴታ

 

1. የክፍል ውስጥ ክትትል (Attendance)

 

1.1.አንድ ሰልጣኝ ሁሉንም የክፍል ውስጥ ትምህርት የላቦራቶሪ የዲሞንስትሬሽንና የስራ ላይ ልምምድን በሙሉ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡ አንድ ሰልጣኝ አንድን ኮርስ በትክክል ተምሮ አጠናቋል የሚባለው 90% የክፍል ውስጥና 95% በስራ ላይ ልምምድና በዲሞንስትሬሽን (ሰርቶ ማሳያ ክፍል) ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ እነዚህን የማያሟላ ተማሪ የሚወስደውን ኮርስ  መድገም ይኖርበታል፡፡ ይህ በብሎክ ሲስተም የሚሰጡ ኮርሶችንም ያጠቃልላል፡፡

 

1.2. ይህንን የማያሟላ ተማሪ አንድ አመት ይደግማል፡፡

 

2. የተማሪዎች የውጤት ቅሬታ አቀራረብና አፈፃፀም (Complaints on Grades):-

 

2.1. ማንኛውም ሰልጣኝ የፈተናዎቹን ውጤት የማየት መብት አለው፡፡ እንዲሁም ማንኛውንም መምህር ለሰልጣኝ ተማሪው የሚሰጠው ውጤት እንዴት እንደተገኘ ለተማሪዎች በግልጽ የማሳወቅ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

 

2.2. ማንኛውንም ሰልጣኝ ባገኘው ውጤት ላይ ቅሬታ ካለው በቀጥታ ከኮርሱ መምህር ጋር በመነጋገር ውጤቱን የማየትና የማጣራት መብት አለው፡፡ መምህሩ ለቀረበው ቅሬታ ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

 

2.3. የትምህርት ክፍሉም የቀረበለትን ቅሬታ በሁለት  ቀናት ጊዜ ውስጥ በራሱ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ግን ተማሪው/ዋ/ በትምህርት ክፍሉ ውሳኔ ካልተስማማ/ች/ ቅሬታውን በጽሑፍ  ለኮሌጁ አ/ም/ዲን አቅርቦ ውሳኔ ያገኛል፡፡ በዚህም ካልረካ አቤቱታ ለዲኑ ያቀርባል፡፡ ዲኑም ወደ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መርተው አስፈላጊውን ማጣራት ተካሂዶበት በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት የመጨረሻውን ውሳኔ ይሰጡበታል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ዲኑ ለአካዳሚክ ኮሚሽን ለውሳኔያ ያቀርቡለታል፡፡

 

2.4. ስህተቱ የመምህሩ ሆኖ ከተገኘ እንደጥፋቱ ክብደትና ቅለት በመምህሩ ላይ የስነ-ስርዓት እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ የሰልጣኙም ሆኖ ከተገኘ በዲሲፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል፡፡

 

 

 

2.5. የመምህሩ ስህተት ሆኖ ከተገኘ መምህሩ ተቀያሪ ውጤት (Grade change Report) አዘጋጆች በአካዳሚክ ኮሚሽን እውቅና በት/ክፍሉ ኃላፊና በኮሌጅ ም/ዲን ካስፈረመ በኋላ ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ያስረክባሉ፡፡

 

ሰልጣኞችን  በተመለከተ

 

3.1. የምክር አገልግሎት (Guidance & Counseling Service)

 

3.2. የትውውቅ መድረክ፡

 

  ሰልጣኞች በተለይም አዲስ ወደ ኮሌጅ የሚገቡ ሰልጣኞችን ልዩ ልዩ ስለኮሌጁ አሰራር ደንቦችና ህጎች፣ ስለ ልዩ ልዩ ክፍሎች አገልግሎት ስለሚጠበቅባቸው መብትና ግዴታዎች በቂ ግንዛቤ እንዲጨ ብጡ ያደርጋል፡፡

 

3.3 የሰልጣኝ መብቶች

 

3.1.1 በዜግነት፣ /በብሄር/ በፆታ፣ በሃይማት፣ በቀለም ወይም በልዩ ፍላጎት ያለው በመሆን ከሚደረግ መድልዎ ነፃ የመሆን መብት፤

 

3.1.2 ሀሳብን በነፃ የማራመድ፣ የመጠየቅ፣ የመከራከርና በማንኛውም ትምህርታዎ ሂደትና ተዛማጅ ተግባራት ውይይት ላይ የመሳተፍ መብት፤

 

3.1.3 የኮሌጁን ደንብ በመከተል በቤተመፃሕፍት፣ ቤተ-ሙከራዎች፣ የኮምፒውተር ማዕከልና በሌሎች አገልግሎቶች /ፋሲሊቲዎች/ የመጠቀም መብት፤

 

3.1.5 የመሰብሰብ፣የመናገር፣ የመፃፍ፣ጹሑፍ የማሳተምና የመደራጀት መብት ኖሯቸው በፖለቲካና ሃይማኖትን በተመለከተ በኮሌጅ ግቢ ውስጥ ምንም መፈፀም አይችሉም፡፡

 

3.1.6 ለሚመለከተው ክፍል በየደረጃው ቅሬታ የማቀርብ ውሳኔ መብት ወይም ፍትሃዊ ያልሆነ ውሳኔ እንዲቀለበስ የመጠየቅ መብት፤

 

3.1.7 ለተከሰሱበት ወይም ለተቀጡበት ጉዳይ መረጃ ማቅረብ/ቅሬታ የማቅረብ መብት/፤

 

3.1.8 እንደወሊድ፣ ሕመም ወይም ከፍተኛ አደጋ ወዘተ ባሉ ችግሮች ትምህርት ቢቋረጥ በኮሌጁ ደንብ መሰረት የመልሶ ቅበላ እድል የማግኘት መብት፤

 

 

 

 

 

3.1.9. አለምንም መድልዎ በትምህርት ተሳትፎና ችሎት የመገምገምና የአመት ወይም በሴሚስተር መጨረሻ የውጤታቸውን ቅጅ የማግኘት መብት፤

 

3.1.10 የኮሌጁን ደንብ መሰረት በማድረግ የፈተና ወረቀቱን ለማስመርመር የማመልከት መብት፡፡

 

3.1.11 የኮሌጁን የት/ፕሮግራም ስለማጠናቀቃቸው የሚገልጽ ሕጋዊ መረጃ የማግኘት መብት፤

 

3.1.12 በሚገጥማቸው የአካዳሚክ ወይም ግላዊ ችግር አስተዳደራዊ እርዳታዎችና የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት፣

 

3.1.13 ሰልጣኞችን የሚመለከት እና የስልጠና ሂደት ለማሳካት የሚቋቋም የተለያዩ ኮሚቴዎች  ላይ የመሳተፍ፡፡

 

3.1.14 የኮሌጁን የትምህርት ስልጠና እድገት እና የመስተዳደር ሁኔታ በተመለከተ ከት/ክፍልና አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር በመሆን ባሉ ችግሮች እና መፍትሔዎች ላይ የመወያየት መብት፤

 

3.1.15. የሚማሩትን እያንዳንዱን ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ከመፈተናቸው በፊት የቲቶሪያል ትምህርት የማግኘት መብት፤

 

3.1.16 ተከታይና ማጠቃለያ ፈተናዎችን የፕሮጀክት ስራዎችን የመውሰድ የፈተናውን እንዲሁም ያገኙትን ውጤት መምህሩ በሚያወጣው ፕሮግራም የማወቅ እና የፈተና ወረቀቶችን ተቀብሎ የማመሳከር መብት፤

 

3.2. የሰልጣኝ ግዴታዎች /ኃላፊነቶች/

 

ተማሪዎች የሚከተሉትን ግዴታዎች ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

3.2.1 የኮሌጁ ህግና ደንብ የማወቅ፣ የማክበርና ተግባራዊ የማድረግ፤

 

3.2.2. እያንዳንዱ ኮርስ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት የመማሪያ ክፍል፣ ለቤተ-ሙከራዎች ወርክ ሾፖች መዘተ የሚያስፈልጉትን የጽፈት መሳሪያዎች ቁሳቁሶችን ሁሉ አሟልቶ የማቅረብ፤


 

3.2.3 በመምህራኖች የሚሰጡ የቤት ስራዎችን፣ የቡድን ስራዎችን፣ የፕሮጀክት ስራዎችን፣ የመስክ ስራዎችን፣ ፈተናዎችን እና የቤተ-ሙከራ ሪፖርቶችን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠናቆ የማቅረብ፤

 

3.2.4 በመደበኛ የትምህርት ካላንደር መሰረት በግንባር በመገኘት የኮሌጁን ሬጅስትራር ጽ/ቤት አመራር ማነጋገር እና የሚፈለግባቸውን ሁሉ የሟሟላት፤

 

3.2.5 የትምህርት አማካሪ መመሪያዎችን እና የሌሎችንም መምህራን ምክር የመቀበል፤

 

3.2.6. የኮሌጁን የትምህርት መሳሪያዎችን እና ሌሎችንም ንብረቶች በጥንቃቄ የመያዝ እና በአግባቡ የመጠቀም፣ የክፍሎችን ንጽህና የመቀመጫዎችን ደህንነት የመጠበቅ፤

 

3.2.7. የኮሌጁን የመምህራን አስተዳደር ኃላፊዎች ትዕዛዝ እና ምክር የማክበር፤

 

3.2.8. ከማንኛውም አደንዛዥ እጽዎች እና ኃላ ቀር ልማዳዊ ተግባራት እራሳቸውን  የማራቅ፤

 

3.2.9. የሌሎችን መብት የማክበር፣ ርስ በርስ መከባበር፣ በሴቶች ላይ የሀይል ጥቃት አለመፈፀም እንዲሁም በማንኛውም የኮሌጁ ማህበረሰብ ላይ የሀይል ጥቃት ለመፈፀም አለመሞከር እና አለመፈፀም፡፡

 

3.2.10. ኮሌጁ የነብስ ወከፍ የሚሰጡ ንብረቶችን በሌላ ያለማስተላለፍ እና ከተፈቀደለት ጊዜ ውጭ በግል ይዞ አለመቆየት፤

 

3.2.11. በኮሌጁ ከተፈቀዱ የሀይማኖት አለባበስ ውጭ በኮሌጁ የተከለከሉ አለባበሶችን  በትምህርት ክፍለ ጊዜ እና በተግባር ልምምድ ጊዜ አለመልበስ፤

 

3.2.12 የራስ ንጽህና የመጠበቅ፣ የምንሰለጥንበትን የሙያ ስርዓት ያለው የአለባበስ ስርዓትን የመከተል፤

 

3.2.13. ለስነ-ስርዓት መጓደል ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርቶች የማድረግ፤

 

3.2.14. ለኮሌጁ እድገት አስፈላጊ ሆኖ ለተገኙ ተግባራት ሁሉ የመሳተፍ፤

 

3.2.15 የመታወቂያ ካርድ የመያዝ እና በተጠየቁ ጊዜ ማሳየት ወይም የመስጠት፤

 

 

 

3.2.16. የቤተ-መጽሐፍት፣ የቤተሙከራ መማሪያ ክፍሎች የመዝናኛ ክበብ ወዘተ ህግና ደንብ የማክበር፤

 

3.2.17 አካባቢን የመንከባከብ እና በግቢ ውስጥ የራስን ድርሻ ማበርከት፤

 

3.2.18. አስፈላጊ በሆነበት ሁሉ ተራ ጠብቆ በሰልፍ የማስተናገድ፤

 

3.2.19. ለፕሮግራሙ ከተመዘገቡ በኋላ በግዴለሽነት ለሚቋረጥ ትምህርት /የመክፈል/

 

3.2.20. በእያንዳንዱ የትምህርት አመት መጨረሻ/ ትምህርትን በሚያቋርጥበት እና በምረቃ ጊዜ ሁሉንም የኮሌጁ ንብረት የመመለስ እና ከመልቀቃቸው በፊት ከንብረት ነፃ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ህጋዊ መረጃ የመያዝ

 

3.2.22.የአገሪቱን ህግ የሚፃረር ማንኛውም አይነት ድርጊት ያለመሳተፍ ወይም ያለመስራት፤

 

3.2.23 የሀገሪቱን የስነ-ምግባር መርሆችን የመተግበር እና የማክበር

 

3.2.24 በስራ ላይ ልምምድ ቦታ እንዲሁም በሰርቶ ማሳያ ክፍል ውስጥ ለትምህርቱ የሚያስፈልጉትን ዩኒፎርም እና ጋዎን ይዞ መገኘት እና የአለባበሱን ደንብ ተከትሎ መልበስ ለምሳሌ፡- የነርስ ሰልጣኞች ቆብ  ማድረግ

 

3.2.25 በተግባር ልምምድ በሚመደቡበት ጤና ድርጅት ሙያዊ ስነ-ምግባር ተላብሶ   መስራት፤

 

3.2.26. የተግባር ልምምድ በሚደረግበት ጤና ድርጅት ታማኝ መሆን ንብረት መጠበቅ ተግባብቶ መስራት፤

 

3.2.27. ወደ ኮሌጁ በተለያዩ ምክንያቶች የኮሌጁ  ማህበረሰብ ያልሆነ አለማስገባት፤

 

3.2.28. በማንኛውም ጊዜ ስብሰባ ማካሄድ ሲፈልጉ በመማክርታቸው አማካኝነት የስብሰባውን አጀንዳ ጊዜና ቦታ በቅድሚያ ለኮሌጁ አሳውቀው ሲፈቀድ ብቻ የማካሄድ፤

 

3.2.29 በጥፋተኝት ላይ ተመርኩዞ በተወሰነ የዲስፕሊን ቅጣት የመፈፀም ግዴታ እና ይህን ሳያጠናቅቁ ከኮሌጁ የሚጠበቅ የግልም ይሁን የቡድን የመብት ጥያቄ አለማቅረብ፤

 

4. የስነ-ስርአት ግድፈቶች (Misconduct)

 

 

 

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰልጣኞች የስነ-ስርዓት ግድፈቶች ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡

 

4.1. በኮሌጅ በየደረጃው የሚገኙ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች የሚተላለፍ የማንኛውም ደንብና መመምሪያ መጣስ፤

 

4.2. የክፍል ውስጥ ትምህርትን ወይም ሌላ መደበኛ የኮሌጁን ፕሮግራም ቀጣይነት ባሉት መልኩ መከታተል አለመቻል፤

 

4.3 የኮሌጁ ወይም ሌሎች የማህበረሰቡን አባላት ስም የሚያጎድፍ ነገር በቃል ወይም በፁሁፍ መበተን ወይም ማሰራጨት እና በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም መዋሸት፤

 

4.5 ታማኝነት የጎደለው ባህሪ ማሳየት ለምሳሌ መስረቅ፣ ማታለል፣ መዋሸት፣ ማጭበርበር የመሳሰሉት፤

 

4.6. በፈተና ማታለል የሌላውን ሀሳብ በፁሁፍ ወዘተ ወስዶ የራስን አስመስሎ ማስተላፍ እና ተዛማች ጥፋት መፈፀም

 

4.7. በነብስወከፍ ወይም በቡድን መደበኛውን ስራ እና ህጋዊ የትምህርት ሂደት ማወክ፤

 

4.8. ያልተፈቀደ አካሄድ /ሂደቶችን መከተል/ ያልተፈቀደ አደረጃጀት ወይም ማንኛውም ያልተፈቀደ የተማሪ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፤

 

4.9. ያልተፈቀዱ እና ህጋዊ ያሆኑ በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎችንም ጹሁፎችን መለጠፍ መበተን፤

 

4.10. የኮሌጁን መጽሀፍት ገጽ በመገንጠል ፣ ላዩ ላይ በመፃፍ፣ በመደበቅ ወዘተ ባግባቡ አለመጠቀም፤

 

4.11. በኮሌጁ ጠረጴዛዎች፣ ግድግዳዎች፣ ወንበሮች እና ቤተ-ሙከራ መሳሪያዎች ላይ መፃፍ፣እንደ ቢላዋ፣ ሽጉጥ፣ ድምጽ የሌላቸው መሳሪያዎች ወዘተ ያሉ አደገኛ መሳሪያዎች ይዞ ወይም ደብቆ  መገኘት፤

 

4.12. ወሲባዊ ትንኮሳ፣ አስገድዶ የመድፈር ሙከራ እና መፈፀም፤

 

4.13. በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ጠጥቶ የመገኘት መስከር፣ ጫትና  ሌሎች አደንዛዥ እጽዎችን መጠቀም፤

 

 

 

4.14. የሰዓት እላፊ ገደብ መጣስ፣ ባልተፈቀደ መግቢያ ላይ ለመግባት መሞከር፤

 

4.15. በማንኛውም ጊዜ የግል መታወቂያ ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት

 

4.16. ሀይማኖታዊ የሆኑ ስነ-ስርዓቶችን በኮሌጁ ቅጥር ጊቢ ማካሄድ፤

 

4.17. ለመማር ማስተማር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥር ሃይማኖታዊ ያልሆነ አለባበስ  ለብሶ  መገኘት፤

 

4.18. የስራ ላይ ልምምድ ዩኒፎርም በደንቡ መሰረት አለመልበስ ማሳጠር እና ሌላ ማስጨመር፤

 

4.19. በኮሌጁ ተለጥፈው የሚገኙ ፖስተሮችን ማስታወቂያዎች መገንጠል እንዲሁም ከላዩ ላይ መፃፍ፤

 

4.20. በቀለም ተማሪ ስልጠናም ይሁን በመስክ ስራ ልምምድ ወቅት በሚኖርበት ማህበረሰብ እና በተመደቡበት ጤና ድርጅት ውስጥ አስነዋሪ ተግባራት መፈፀም ለምሳሌ መደባደብ የቤት ኪራይ በወቅቱ አለመክፈል እና የመሳሰሉትን ግድፈቶችን መፈፀም፤

 

4.21. ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ የስነ-ምግባር ችግሮች ሆኖ ሊጠቀሱ የሚችሉ ተግባራትን እና አጠቃላይ የአንቀጽ 5.3 የተጠቀሱትን የሰልጣኝ ግዴታ አለመፈፀም፤

 

5. የስነ-ስርዓት እርምጃዎች (Disciplinary Actions):-

 

የተማሪዎችን የስነ-ስርዓት (Discipline) ኮሚቴ በዚህ አንቀጽ 5.6 የስነ ስርዓት አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት የስነ-ስርዓት ግድፈቶች የሚሰጠው የቅጣት አይነት የመወሰን የውሳኔ ሀሳብ  ለዲኑ ያቀርባል፡፡ የውሳኔው ሀሳብ ተፈፃሚ የሚሆነው የኮሌጁን ዲን መርምረው ሲያፀድቁት ብቻ ይሆናል፡፡

 

5.1. የሰልጣኞች የስነ-ስርዓት ኮሚቴ

 

   5.1.1 የተማሪዎች ዲስፒሊን ቋሚ ኮሚቴ (Students Disciplinary Standing Committee)

 

ሀ/ የኮሚቴው አስተዋጽኦ

 

·         በዲን የሚመረጥ --------------------------------- ሰብሳቢ

 

·         የተማሪዎች መማክርት 2 ተወካዮች /አንዷ ሴት/ ለቀን ተማሪዎች ጉዳይ ብቻ -------- አባል

 

 

 

·         የማታ ተማሪዎች 2 ተወካይ /አንድ ሴት/ ለማታ ተማሪዎች ብቻ --------- አባል

 

·         የአስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ --------------- አባልና ፀሐፊ

 

ለ/ ተግባር እና ኃላፊነት

 

1. ከተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ ጋር በመሆን በተማሪዎች የኮሌጁን የስነ-ምግባርና ስነ-ስርዓት ደንቦችን ያስተዋውቃል፡፡ አበክረው እንዲማሩ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፡፡

 

2. ጥፋት በሚፈጽሙ ተማሪዎች ላይ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች በመመሪያው መሰረት እንዲፈፀም የውሳኔ ሀሳብ በዲኑ ወይም በአካዳሚክ ኮሚሽኑ ያቀርባል፡፡ ዲኑ የውሳኔ ሀሳቡን  መርምሮ ማፅደቅ ወይም ማሻሻል እና ኮሚቴው እንደገና በማየት የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ያደርጋሉ፡፡

 

3.  በተጨማሪ ከስነ-ስርዓት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት ያከናውናሉ፡፡

 

ሐ/ በሰልጣኞች ላይ ክስ አመሰራረት

 

·         ሰልጣኞች በፈፀሙት የስነ-ስርዓት ግድፈት በዲስፕሊን ኮሚቴ ጉዳዩ እንዲታዩ የሚደረገው ዲኑ ይም የዲኖቹ የጋራ ፎርም ሲታመንበት ብቻ ነው፡፡

 

·         ክሱም ለዲስፕሊን ኮሚቴው የሚያቀርበው የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊው ይሆናል፡፡

 

5.1.2 የኮሚቴው ተጠሪነት

 

ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለኮሌጁ ዲን ይሆናል

 

5.1.3 የኮሚቴው የስራ ዘመን

 

የስነ-ስርዓት ኮሚቴው ለሁለት  ተከታታይ የትምህርት ዓመታት  በኃላፊነት ይቆያል፡፡ ሆኖም ግን  የስነ-ምግባር ችግር ያለበት የኮሚቴው አባል በማንኛውም ጊዜ ከኮሚቴው አባልነቱ ይወርዳል፡፡ አባሉም ከኮሚቴው እንዲወርድ የሚወስኑት ዲኑ ወይም በዲኖች ፎርም ታይቶ ይሆናል፡፡

 

5.1.4. የቅጣት አይነቶች

 

5.1.4.1 በተደጋጋሚ ቀላል ጥፋቶች ግለቢስ እንዲያደርጉ ማድረግ

 

5.1.4.2 የቃል ወይም የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት፡፡

 

5.1.4.3 ያበላሹት ወይም ያጠፉትን ንብረት እንዲተኩ ወይም ግምቱን እንዲከፍሉ ማድረግ፡፡

 

 

 

5.1.4.4 ለአንድ አመት ከኮሌጁ እንዲታገዱ ማድረግ፡፡

 

5.1.4.5 ለፈፀሙት ተደጋጋሚ እና ከፍተኛ ጥፋት እስከመጨረሻው ማስወገድ ወይም ከኮሌጁ ማሰናበት፡፡

 

5.1.4.6 ማንኛውም የስነ-ስርዓት ግድፈት የፈፀመ ሰልጣኝ ስምና የተወሰደውን የእርምት እርምጃ በግልጽ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋል፡፡

 

 

 

የተማሪዎች ስነ-ስርዓት ግድፈት ደረጃዎች

 

 5.2.1. የመጀመሪያ ደረጃ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች

 

 5.2.1 ቤተ መፅሐፍት ውስጥ ማስቲካ ማኘክ፣ ድምጽ ማሰማት፤

 

       5.1.2.1. ቤተ -መጽሐፍት ውስጥ ድምጽ የሚያሰማ ጫማ አድረጎ መግባት፣

 

 5.2.1.2. የቤተ-መጽሐፍት ጽሁፎች ስር ማስመር መጽሐፍቶች ላይ መፃፍ፣

 

       5.2.1.3. ተንቀሳቃሽ ስልከ መማሪያ ክፍል ወይም ቤተ መጽሀፍት ውስጥ ይዞ መግባት

 

               ፀጥታን ማወክ

 

       5.2.1.4. በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ ፀጥታን የሚያውኩ ተግባራትን መፈፀም ለምሳሌ፡-

 

              መጮህ፣ ማፏጨት የመሳሰሉት፣

 

      5.2.1.5. የስራ ልምምድ ዩኒፎርም በአግባቡ አሟልቶ አለመልበስ፣ ማሳጠር ወይም ሌላ

 

              ማስጨመር

 

      5.2.1.6. ሌሎች ቀላል ተብለው ለፈረጁ የሚችሉ ጥፋቶችን ፈፅሞ መገኘት

 

5.2.2. ሁለተኛ ደረጃ የስነ-ስርአት ግድፈቶች

 

          5.2.2.1. በንዑስ አንቀጽ 5.7.1 ከቁጥር 5.7.1.1 እስከ 5.7.1.7 የተመለከቱትን

 

                  የስነ-ስርዓት ጥፋቶችን ለሁለተኛ ጊዜ የፈፀመ፣

 

         5.2.2.2 ለመማር ማስተማር ሂደት እና ለመስክ ስራ ልምምድ አስቸጋሪ የሆኑ ሀይማኖታዊ

 

  ወይም ሀየማኖት የሆኑ አለባበሶችን ለብሰው በኮሌጁ ግቢ ወይም በተግባ ልምምድ ቦታ ላይ መገኘት 

 

           5.2.2.3. በኮሌጁ ተለጥፈው የሚገኙ ፖስተሮችን ማስታወቂያዎችን መገንጠል፣ ወይም ላይ መፃፍ

 

                5.2.2.4. የፈተና ማታለል ለምሳሌ በፈተና ወቅት እጅ ላይ ፅፈው በመግባት፣ ወረቀት ይዞ

 

መግባት፣ ከሌሎች ለመቅዳት መሞከር እና የፈተናውን አሰጣጥ ሂደት የማወክ ተግባራት መፈጸም

 

         5.2.2.5. የኮሌጁን መጽሐፍቶች ከተቀመጡበት አንስቶ መደበቅና ሌሎች እንዳይተቀሙበት

 

                  ማድረግ

 

         5.2.3. 3ኛ ደረጃ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች

 

         5.2.3.1. የንዑስ አንቀፅ 5.7.2.1 የተጠቀሰውን በ3ኛ ጊዜ የፈፀመና በቁጥር 5.7.2.6.

 

              ድረስ ያሉት የስነ- ስርዓት ግድፈቶችን ለሁለተኛ ጊዜ የፈፀመ

 

5.2.3.3. በኮሌጅ ደረጃ ሚገኙ የአካዳሚክ እና አስተዳደር ኃላፊዎች ሚተላለፍ ማንኛውም ደንብ እና መመሪያ መጣስ

 

5.2.3.3. የክፍል ውስጥ ትምህርትን መደበኛ የኮሌጁ ፕሮግራሞች ቀጣይነት ባለው መልኩ መከታተል አለመቻል ወይም ሌሎች እንዳይከታተሉ ማድረግ

 

5.2.3.4. የኮሌጁን ወይም ሌሎችን የማህበረሰቡን ስም የሚያጎድፍ ተግባራትን በቃል መፈፀም ወይም  በጹሁፍ መበተን ዌይም ማሰራጨት በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም መዋሸት

 

5.2.3.5. በሰልጣኞችም ላይ ይሁን በአካዳሚክ አስተዳደር ሰራተኞች ላይ አግባብ ያልሆነ ባህሪ ማሳየት፣ ሀይል ለመጠቀም መሞከር፣ በመበጥበጥ የድብደባ ሙከራ ማድረግ እና መደባደብ

 

 

 

 

 

5.2.3.6. ታማኝነት የጎደላቸው ተግባራት ማሳየት እና መፈፀም ለምሳሌ፡- መስረቅ፣መዋሸት ፣ ማታለል

 

5.2.3.7. የሌላውን ሀሳብ ጹሑፍ ወዘተ ወስዶ የራስ አሰመስሎ ማሰተላለፍ እና ተዛማች ጥፋት መፈፀም

 

5.2.3.8. የነፍስ ወከፍ ወይም ማንኛውንም ያልተፈቀደ የተማሪ ስብሰባ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ

 

5.2.3.9. ያልተፈቀደ አደረጃጀት ወይም ማንኛውም ያልተፈቀደ የተማሪ ስብሰባ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ

 

5.2.3.10. ያልተፈቀዱ እና ህጋዊ ያልሆኑ በራሪ ወረቀቶች እና ጽሁፎችን መለጠፍ ወይም መበተን

 

5.2.3.11. የኮሌጁን መጽሀፍት ገጽ መገንጠል

 

5.2.3.12. እንደ ሽጉጥ ቢላዋ ሌሎች ድምፅ የሌላቸውን አደገኛ መሳሪያዎችን ይዞ ወይም ደብቆ መገኘት

 

5.2.3.14. የኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጠጥቶ ወይም ሰክሮ መገኘት ጫትና ሌሎችንም አደንዛዥ ዕፆችን መጠቀም

 

5.2.3.15. የሰዓት እላፊ ገደብ መጣስ

 

5.2.3.16. ባልተፈቀደ መግቢያ ለመግባት መሞከር

 

5.2.3.17. በማንኛውም ግዜ የግል መታወቂያ ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት

 

5.2.3.18. ሀይማኖታዊ የሆኑ ስነ-ስርዐቶችን በኮሌጅ ቅጥር ግቢ ማካሄድ

 

5.2.3.19. ለመስክ ስራ ልምምድ በተመደቡበት ተቋም ሰራተኞች መዝለፍ ወይም ግጭት መፍጠር እና  በተመደቡበት ጤና ድርጅት ውስጥ አስነዋሪ ተግባራትን መፈፀም

 

         ለምሳሌ፡- አስገድዶ መድፈርና ሙከራ ሌሎችንም

 

 

5.2.3.20. በቀለም ትምህርት ስልጠና ይሁን በመስክ ስራ ልምምድ ወቅት በሌሎች ማህበረሰብ ለምሳሌ፡- የቤት ኪራይ አለመክፈል ፍርድ ቤት ተረጋግጦ ለኮሌጁ ሲደርሰው ተፈፃሚ የሚደረግ ይሆናል፡፡

 

5.2.3.21. ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ የስነ-ምግባር ችግሮች ውስጥ በ3ኛ ደረጃ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች ሆነው ሊጠቀሱ የሚችሉ ተግባራት እና በአጠቃላይ በአንቀፅ 5-3 የተጠቀሱ ግዴታዎችን አለመፈጸም

 

5.4. በተማሪዎች ላይ በየደረጃው ሊወሰዱ የሚገባቸው የሰነ-ሰርዓት እርምጃዎች

 

5.4.1. ለመጀመሪያ ጊዜ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች የሚወሰዱ እርምጃዎች የጥፋት ዓይነት ከቁጥር 5.7.1.1 እስከ ቁጥር 5.7.1.ገ እና 5.7.2.3. ያሉትን የስነ -ስርዓት ግድፈቶች የፈፀሙ 

 

የሚወሰዱ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች

 

ሀ) ግለሂስ እንዲያደርጉ ማድረግ ተግሳጽ ወይም የቃል ማስጠንቀቂያ

 

 5.4.2. ለሁለተኛ ደረጃ ግድፈቶች የሚወሰዱ እርምጃዎችና የጥፋት አይነቶች               

 

     ሀ) የመጀመሪያ ደረጃ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች ለ2ኛ ጊዜ የፈፀሙ

 

     ለ) ለመጀመሪያ ጊዜ ከተራ ቁጥር 5.7.2.1. እስከ 5.7.2.2. እና 5.7.2.5.7. ግድፈቶችን የፈፀሙ

 

የሚወሰዱ የሰነ-ስርዓት እርምጃዎች

 

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ

 

5.4.3. ለ3ኛ እርምጃ የስነ-ስርዓት የሚወሰዱ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች፡-

 

     ሀ) የጥፋት ዓይነት

 

 ለሦስተኛ ጊዜ በተራ ቁጥር 5.8.2. ሀ እና ለ2ኛ ጊዜ በተራ ቁጥር 5.8.8.2 ላይ የተመለከቱት ግድፈቶችኝ የፈፀመ እንዲሁም በቁጥር 5.7.2.4 እና 5.7.2.6 ከቁጥር 5.7.3.1 እስከ ቁጥር 5.7.3.4. ከቁጥር 5.7.3.7. እስከ ቁጥር 5.7.3.11. እና ከቁጥር 5.7.3.15. እስከ ቁጥር 5.7.3.19 ድረስ እና ቀጥር 5.3.21 እና 5.3.21. እና 5.3.22 ድረስ የተመለከቱትን የስነ-ስርዓት ግድፈቶች  ለመጀመሪያ ግዜ የፈፀመ

 

 

የሚወሰዱ ስነ-ስርዓት እርምጃዎች

 

ለ1 አመት ከትምህርት ማዘግየት

 

ሀ/ የጥፋት አይነት

 

ለ/ በቁጥር 5.7.35 እና 5.7.3.6 የተመለከቱትን እና ከቁጥር 5.7.3.12 እስከ 5.7.3.14 እና ቁጥር 5.7.3.2.0 የተመለከቱትን የስነ-ስርዓት ግድፈቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀመ እና

 

ሐ/ ከቁጥር 5.8.3 የተፈፀመውን ጥፋቶች ፈጽሞ ከ1 አመት የትምህርት ገበታ ታግዶ እንደገና ወደ ኮሌጁ የገባ ሰልጣኝ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ ጥፋቶችን አጥፍቶ ከተገኘ፡-

 

የሚወሰዱ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች

 

ከኮሌጁ ማሰናበት

 

5.4.4 ከላይ የተዘረዘሩትን የስነ-ስርዓት እርምጃዎች ደረጃቸውን ጠብቀው መወሰድ ያለባቸው መሆኑን ይታመናል፡፡ ይሁን እንጂ የስነ-ስርዓት ኮሚቴው እንደ ጥፋቱ ደረጃ ሳይጠብቅ የመጨረሻውን የውሳኔ ሀሳብ ለኮሌጁ ዲን ሊያቀርበው ይችላል፡፡

 

 

 

Go to top